call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

የሕጻናት ማህበራዊ እድገት

ሕጻናት ማህበራዊ እድገታቻው ይበልጥ እየዳበረ ሲመጣ በቡድን ተደራጅተው የተለያዩ የስራ እቅዶችን ይወጥናሉ፡፡ ሕጻናት እቅድን በቡድን በመተግበር ውጤት ለማምጣት ይጥራሉ፡፡ ለምሣሌ በጣም ትንሽ የእርሻ ቦታን በመፍጠር ከሸክላ አፈርና ከጭቃ የተለያዩ የእንስሳት ቅርፆችን ይሰራሉ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ ሕጻን ላልተለመደ ወይም እንግዳ ነገር ያለውን አስተያየት ወይም ምላሽ በማስተዋል ስለ እድገቱ ሁኔታ ልንረዳ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሕጻን መጀመሪያ አንድን ቁስ በመፈተሽ ስለ ምንነቱ ማጥናትና ማወቅ ይፈልግ ይሆናል፡፡ ለማረጋገጥ ቁሱን ወደ አፉ ይወስዳል፡፡ በእድሜ ትንሽ ከፍ ያለው ሕጻን ደግሞ በዕቃው ውስጥ ያለውን ነገር ለማወቅ በተለየ ሁኔታ ያወዘውዛል፣ ያንከባልላል፣ ይገፋል፣  ከፍ-ዝቅ ያደርጋል ያንቀሳቅሳል፡፡ የአምስትና ስድስት ዓመት ሕጻን ይህን ቁስ ለይቶ ለመመደብ የተሻለ ግንዛቤ አለው፡፡ በዚህ እድሜ ክልል የሚገኝ ሕጻን በስሜት ሕዋሳቱ አማካኝነት ነገሩ የት እንደሚመደብና ለምን ዓላማ እንደታቀደ ይረዳል፣ ይገነዘባል፡፡ ቁሱ አደገኛና ችግር ፈጣሪ ከሆነ ይህንን የማወቅ ችሎታ ስላለው ለመምህሩና በዙሪያው ላለ ዓዋቂ ሰው ያስረክባል፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን አጠቃላዩ የሕጻናት እድገት ሂደት መሠረታዊ ተመሳሳይነት ቢታይበትም እያንዳንዱ ሕጻን ከሌላው የተለዬ ስብዕና ያለው መሆኑን እንርሳ፡፡

መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!

ሣህሉ ባዬ ዓለሙ

www.enrichmentcenters.org

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”