call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

4 Years old child

የ 4 ዓመት ሕጻናት ባህርያት፡-

ሕጻናት እድሚያቸው አራተኛ ዓመት ላይ ሲደርስ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ እራሳቸውን የመቆጣጠር፣ የመስጠትና የመቀበል ብቃት ማሳየት ይጀምራሉ፡፡ ይህ እድሜ ድርሻ የመውሰድና የመጋራት፣ የሌላውን ስሜት የመካፈል ጠባያትን መማር የሚያዳብሩበት እድሜያቸው ነው፡፡ አሁን ከሌሎች ሕጻናት ጋር የመጫወት ፍላጐታቸውና ችሎታቸው እያደገና እየጨመረ መጥቷል፡፡ የሕጻናት ስብዕና እንዲያብብና ፈክቶ ፍሬ እንዲያፈራ  ለእያንዳንዱ ሙከራ ማመስገን፣ ማድነቅና ማበረታታት ተገቢ ነው፡፡ ይሁን እንጅ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕጻናት ግልፅ የሆነ የማሰብ ችሎታ ተጠቅመው ከገደብ የመውጣት አዝማሚያን በቃላትና በተግባር ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ ሕጻናት የመማር ደንበሮች አሏቸው፡፡ ይህ የእድሜ ክልል ታላላቅ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚፈልቁበት የእድሜ ክልል ነው፡፡ “እንዴት?” እ“ለምን?” የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያቀርቡበት፣ ለነገሮች መግለጫ፣ ማብራሪያና መረጃ የሚጠይበት የዕድሜ ክልል ነው፡፡ የአራት ዓመት ሕጻናት በርካታ ተግባራትን ማከናወን ይማራሉ ወይም ለማከናወን ይጥራሉ፡፡አንዳንዴ ሕጻናት በሥራ ስለሚደክሙ ደስታ ፈጣሪ ዜናዎቻቸውን ለሚያዳምጣቸው ሰዎች ሁሉ ማካፈል ይፈልጋሉ፡፡ ከአንደበታቸው የሚወጡ ቃላት “ጉራ በኪሴ” አይነት ያስመስሏቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሕጻን ስለ ሁኔታው እንዲህ በማለት ለአድማጩ ይገልጻል፡፡ “ተመልከቱኝ! ከዚህ ቅርንጫፍ ላይ መወዛወዝ እችላለሁ!”፣“ማፏጨት እችላለሁ!”፣ “መስማት ትፈልጋላችሁ? ዛሬ ልብሴን የለበስኩት እኔ እራሴ ነኝ! ማንም የረዳኝ የለም!” በማለት የአድማጩን ትኩረት ለመሳብ ይጥራል፡፡ ሆኖም ሕጻኑ በሀቅ እየፎከረ አይደለም፡፡ ይልቁን እነዚህን ተግባራት ማከናወኑና ለማከናወን መብቃቱን በእጅጉ ማመን ስላቃተው ነው፡፡ ለሕጻናት “ትልቅ” የመሆን ስሜት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ በዙሪያቸው የተዘጋጁ ነገሮች ሁሉ ለትላልቅና አዋቂ ሰዎች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በሮች፣ እጀታዎች፣ ጠረጴዛዎችና ወንበሮችን ያጤኗል፡፡ አንዳንዴ በመስኮት ወደ ውጪ ለመመልከት ሲፈልጉ ወንበር ላይ ለመንጠላጠል ይገደዳሉ፡፡ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ የማድረጉ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕጻኑን ሙከራና ጥረት ማበረታታት ግን ጠቃሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሚሰጠው ማበረታቻ ለሁሉም ሙከራዎች አንድ ጊዜ ብቻ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰጠው ማበረታቻ እያንዳንዱ አዲስ የተናጠል ሙከራ ወይም ጥረት ከሚያስከትለው ደስታና ጥንቃቄ ጋር የተዛምደ መሆን ይኖርበታል፡፡

ዓመታት እየተቆጠሩና የሕጻናት ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ ፍላጎታቸው በሚገርም ሁኔታ እየጨመረና እየሰፉ ይመጣል፡፡ የማሰብ ችሎታቸው ከወትሮው በተለየ መልኩ ይበልጥ በተጨባጭና በምክንያታዊ ጥያቄዎች የተሞላ ይሆናል፡፡ አሁን ሕጻናት እራሳቸውን ለመቆጣጠር ዝግጁ ስለሆኑ ከዚህ በኋላ ገደባቸውን አይዘሉም፡፡ አሁን የሕጻናት አካላዊ እንቅስቃሴ በሂደት እየተቀናጀ መጥቷል፡፡ በማሕበራዊ ባህርያቸው እቅዶችን በጋራ አውጥቶ የሚተገብር ቡድን አላቸው፡፡ ሕጻናት ካለፈው ጊዜ በተሻለ ከሁኔታዎች ጋር እራሳቸውን የመለወጥና የማጣጣም ባህርይ አላቸው፡፡ እንዲህም እያለ የሕፃናት ዕድገት ይቀጥላል፡፡ በሰባት ዓመታቸው አካባቢ ወደ መደበኛ ትምህርት ይሸጋገራሉ፡፡

 

መልካም፣ መልካሙን ለሕጻናት!

ሳህሉ ባዬ

www.enrichmentcenters.org

 

 

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”